ስለ ቆ.ኢ.ል.ኢ

ራዕይና ተልዕኮ
ኢንስቲትዩቱን ውጤታማ ተቋም በማድረግ በ2015 የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ በአለም አቀፍ ያለውን የገበያ ድርሻ በ 10 እጥፍ አድጎ ማየት፣

ራዕይ

የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪን ዘላቂና ፈጣን በሆነ መልኩ ኢንዲስፋፋ በማድረግ በኢንቨስትመንት፣ በምርትና በግብይት ለልማታዊ ባለሀብቱ ቀልጣፋ የቴክኖሎጂ፣ የምክር አገልግሎትና ድጋፍ በመስጠት አገሪቷ ከቆዳ ሀብቷ ከፍተኛ ተጠቃሚ እንድትሆን ማድረግ፣

የኢንስቲትዩቱ ዓላማ

የቆዳ አና ቆዳ ዉጤቶች ኢንዱስትሪዎች ቴክኖሎጂዎች ልማትንና ሽግግርን በማፋጠን ኢንዱስትሪዎቹ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ፈጣን ልማት እንዲያስመዘግቡ ማብቃት ይሆናል፡፡

ዕሴቶች
 • ደንበኛ ተኮር አገልግሎት
 • ለለውጥ ዝግጁነት
 • የላቀና ፍትሃዊ አገልግሎት
 • ቅንጅታዊ የቡድን አሠራር
 • ሙያዊ ሥነ-ምግባር
 • ለአካባቢ ደህንነትና ክብካቤ ተቆርቋሪነት
 • ምቹ የሥራ ከባቢያዎች ሁኔታዎች መፍጠር
ድርጅታዊ መዋቅር
የኢንስቲትዩቱ ተግባርና ኃላፊነት

የኢንስቲትዩቱ ተግባርና ኃላፊነቶች የሚከተሉት ናቸዉ:

 • የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች ልማትን ለማፋጠን የሚረዱ ፓሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና መርሐ-ግብሮችን ማዘጋጀት፣ ሲፈቀዱም ተግባራዊ ማድረግ፣

 • የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች ልማት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ መተንተን፣ ማደራጀት፣ ለዘርፉ የመረጃ ማዕከል ማስተላለፍና እንደ አስፈላጊነቱ ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት፣

 • የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የሚያስችሉ የፕሮጀክት ፕሮፋይሎችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት፣ ወደ ዘርፉ ለሚገቡ ባለሀብቶች የአዋጭነት ጥናት ማድረግ፣ በፕሮጀክት አፈፃፀም ላይ ክትትል ማድረግ እና በአፈፃፀም ላይ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ መስጠት፣

 • በቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች በቴክኖሎጂ መረጣ፣ በድርድር፣ በግንባታ፣ በተከላና በሙከራ ምርት የምክር ድጋፍ መስጠት፣

 • የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች የዘርፉን ልማት የሚያግዙና ዘርፉን ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የቴክኖሎጂ፣ የቴክኒክ፣ የግብይት፣ የስራ አመራርና ሌሎች እንደ አስፈላጊነቱ የሚዘጋጁ ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን ማዘጋጀትና መስጠት፣ ለሠልጣኞችም የምስክር ወረቀት መስጠት፣

 • የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች ዘርፉን ለማሳደግ የሚያግዙ የጥናትና የምርምር ሥራዎችን ማከናወን፣

 • በምርት ሂደት፣ በምርት ዕቅድና በጥራት ቁጥጥር ላይ ድጋፍና የማማከር አገልግሎት መስጠት፣

 • የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች ልማትን ሊያፋጥኑና ተወዳዳሪ ሊያደርጉ የሚችሉ የምርጥ ተሞክሮዎች ጥናት ማካሄድና በዘርፉ ተመሳሳይ ተግባር የሚያከናውኑትን መደገፍ፣

 • ለቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች የግብዓትና የምርት ትስስር እንዲፈጠር ድጋፍ መስጠት፣

 • ለቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪዎች ምርቶች የገበያ ጥናቶችን ማከናወን፣

 • ሊለሙ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን መለየትና የምርት ልማት ሥራ ማከናወን፣

 • ከዩኒቨርስቲዎች ጋር የምርት ልማትንና የሰው ኃይል ልማትን በተመለከተ በመተባበር ይሰራል፣ በጋራ የምርምር ሥራዎችን ያካሂዳል እንዲሁም በዘርፉ የሀገር ውስጥ የምርምር አቅም እንዲጠናከር ያግዛል፣

 • ለተጠቃሚዎች የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል መስጠት፣

 • ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች እንደአግባቡ ክፍያ መጠየቅ፣

 • የንብረት ባለቤት መሆን፣ ውል ማዋዋል፣ በራሱ ስም መክሰስና መከሰስ፣

 • ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባሮችን ማከናወን፡፡