ኦዲት እና ኢንስፔክሽንራዕይ
 • ዉጤታማ የሀብት አጠቃቀምን በማረጋገጥ'የምከርና የአፈፃጸም ክትትል ሥራዎችን በማከናወን ለኢንስቲትዩቱ ተጨማሪ እሴት (Value) በምፈፅር መልኩ እገዛ በማድረግ በ2015 የቆዳ ኢንዱስትሪን ገቢ በ10 እጥፍ አድጎ ማየት'
ተልዕኮ
 • የኢንስቲትዩቱን የበጀት ፣ የፋይናንስና የንብረት አያያዝና አጠቃቀም ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን፣ የሰው ሀብት አስተዳደር ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በተገቢ ሁኔታ ተፈፃሚ መደረጋቸውን፣ በሥራ አመራሩ የተዘረጉ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓቶች በቂና አስተማማኝ መሆናቸውን፣ የሥራ አፈጻጸሞች ኢኮኖሚያዊ ዉጤታማና ስኬታማ መሆናቸውን የማረጋገጥ፣ ሥራዎች እንዲሻሻሉ ሙያዊ የምክር ድጋፎች መስጠትና የመፍትሔ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በሥራ አመራሩ ውሳኔ የተላለፈባቸውን ጉዳዮች ስለአፈፃጸማቸው የክትትል ሥራዎች በማከናወን ለበላይ አመራር ለውሳኔ የሚረዳ የመፍትሔ ሃሳቦችን ማቅረብ ነው፡፡
ዋና ዋና ተግባራት
 • የፋይናንስ ምዝገባዎች' መረጃዎችና ሰነዶች ትክክለኛነት ማረጋገጥ
 • የንብረት አያያዝና አጠቃቀም ምዝገባዎች ' መረጃዎችና ሰነዶች ትክክለኛነት ማረጋገጥ
 • የፋይናንስና የንብረት አያያዝና አጠቃቀም ፖሊሲዎች'አዋጆች'ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን፣የሰው ሀብት አስተዳደር ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች አፈፃጸምን ማረጋገጥ
 • በፋይናንስ በንብረትና በሥራ አፈፃጸሞች ላይ የተዘረጉ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ብቃትና አስተማማኝነት ማረጋገጥ
 • የሥራ አፈፃጸም ኢኮኖሚያዊ ውጤታማነትና ስከታማነትን በመገምገም የደንበኛ እርካታን ማረጋገጥ
 • ክፍተቶችን በመለየት የምክርና የአፈፃጸም ክትትሎችን በማከናወን ሥራዎች እንዲሻሻሉ የመፍትሔዎችን ሃሳቦችን ማመንጨት
እሴቶች
 • ሕጋዊና ኢኮኖሚያዊ የሀብት አስተዳደር ሥርዓት ማስፈን
 • አጋዥነት/አጋርነት (Partnership)
 • ተጠያቂነት (Accountability)
 • ምላሽ ሰጪነት (Responsiveness)
 • ደንበኛ ተኮር አገልግሎት