የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

የህዝብ ግንኙነት አካላት ተግባርና ኃላፊነቶች


 • የመንግሥት ፖሊሲዎችን፤ ስትራቴጂዎችንና ልዩ ልዩ የልማት ፕሮግራሞችን በተመለከተ ብሄራዊ መግባበትንና የገጽታ ግንባታን ለመፍጠር ሁነቶችን ማደራጀት፣ የምክክርና የውይይት መድረኮች ማዘጋጀት፣ማቀናጀትና ማመቻቸት
 • በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መልዕክቶችንና ፕሮግራሞችን በመቅረጽ በሚዲያ እንዲተላለፉ ማድረግ
 • የሚዲያ ሞኒተሪንግ እና የከባቢያዊ ሁኔታ ቅኝት ስራዎችን ማከናወን
 • የጋዜጣዊ ጉባዔ፤የጋዜጣዊ መግለጫና የኤግዝቢሽን ሥራዎችን ማስፈጸም፣የምክክር መድረኮችን፣ የስራ ጉብኝቶችንና ቃለ ምልልሶችን ማዘጋጀትና ማስተባበር እንዲሁም የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ ማድረግ
 • የቃል አቀባይነት ስራዎችን ማከናወን
 • ኢንስቲትዩቱንና የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፉን በተመለከተ ቀውሶች እንዳይከሰቱ አስቀድሞ መከላከልና ከተከሰቱም መከላከል
 • የኢንስቲትዩቱን አገልግሎት አሰጣጥ ለ ደነንበኘኞችነና ለባለ ድርሻ አካላት እንዲሁም ለህዝብ ማስተዋወቅ
 • የኢንስቲትዩቱን ራዕይ፤ ተልዕኮ፤ እሴት፤ ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ለደንበኞች የተለያዩ የኮሙኒኬሽን መሣሪያዎችን በመጠቀም ማስተዋወቅ
 • የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍን አሰስመለልከክተቶ መነንገግሰስተት በየወቀቅተቱ የሚያወጣቸውን አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች በተገለልገጋየዮቸች ዘንድ ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ
 • የኢንስቲትዩቱንና የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፉን የስራ እንቅስቃሴዎች በኦዴቪዥዋል መሳሪያዎች ቀርፆ በተለያየ ዘዴ ለተጠቃሚዎች ማድረስ
 • የኢንስቲትዩቱንና የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፉን የስራ እንቅስቃሴዎች አስመልክቶ ከህዝብ ለሚቀርቡ ጥያዌዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠት
 • የሚዲያ ግንኙነት ሥራዎችን ማከናወን
 • የኢንስቲትዩቱን ዓላማና የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፉን የየወቅቱን የሥራ እንቅስቃሴ የሚገልጹ መጽሄቶች፣ ዜና መጽሄቶች፣ ብሮሸሮች፣ በራሪ ጽሁፎችንና ፖስተሮችን እንዲዘጋጁና እንዲሰራጩ ማድረግ