የኢንጂነሪንግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
ተልዕኮ
የኢንጅነሪንግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተልዕኮ የቆዳ ኢንዱስትሪዉ ተዓማኒነት ያለዉና ሞያዊ የሆነ አገልግሎትን በመስጠት የደንበኞቹን ፍላጎት እንዲያሟላ የተለያዩ የኢንጂነሪንግ አገልግሎቶችን መስጠት ሲሆን በፈጠራ የታገዙና ጥራት ያላቸዉ የተለያዩ የኢንጂነሪንግ ዘርፍ ድጋፎችን ይሰጣል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ ዘርፈ ብዙ የሆኑትን እነዚህን አገልግሎቶች በአንድ መስኮት አሰራር ነዉ የሚሰጠዉ፡፡ የዳይሬክቶሬቱ ዋነኛ አላማ የኢትዮጵያን የቆዳ ኢንዱስትሪ በአጠቃላይ እንዲሁም ወደ ዘርፉ የሚቀላቀሉ አዳዲስ ባለሀብቶችን በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የተለያዩ የኢንጂነሪንግ የእዉቀት ዘርፎን ፣ ቁሳቁሶችን ፣ ባለሞያዎችን ፣ ዘዴዎችን ፣ አቅሞችንና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም መደገፍ ነዉ፡፡ የዳይሬክቶሬቱ ዋነኛ ጠቀሜታም ለቆዳ ኢንዱስትሪዉ ዘርፍ ቀጣይነት ያለዉ፣ ተጨባጭና ተፈላጊ የኢንጂነሪንግ አገልግሎትን መስጠት ነዉ፡፡