የኢንጂነሪንግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

አገልግሎት


በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች፡-
  • ባለሀብቶችና በየደረጃዉ ያሉ ወሳኝ አካላት መዋዕለ ነዋያቸዉን በዘርፉ እንዲያፈሱ ዉሳኔ ላይ እንዲደርሱ የሚያስችል የተሟላ መረጃ መስጠት
  • ፕሮጀክት ፕሮፋይሎችን ማዘጋጀትና ማስተዋወቅ፣ በተለያ ዘርፎች ያለዉን የኢንቨስትመንት እድል በተመለከተ የቅድመ ኢንቨስትመት አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችል ፣ ፕሮጀክቶችን ለመለየትና ወደ ዘርፉ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች የአዋጭነት ጥናት ማካሄድ
  • ባለሀብቶችን በቴክኖሎጂ መረጣ፣ በድርድር ፣ በማሽን ተከላና ዝርጋታ ፣ በኮሚሽኒንግና በፋብሪካ ግንባታ ረገድ መደገፍና ማማከር
  • የፕሮጀክቶችን ትግበራ መከታተልና በትግበራ ወቅት ላጋጠሙ ችግሮች መፍትሄዎችን መፈለግ
  • ለፋብሪካዎች የቴክኒክና የጥገና ድጋፍ መስጠት
  • የኢፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ድጋፍ

በዳይሬክቶሬቱ ስር የሚገኙ የመስሪያ ግብዓቶች
  • ሜካኒካል ወርክሾፕ
  • ኤሌክትሪካል ወርክሾፕ
  • የእንጨት ስራ ወርክሾፕ