ያካባቢ ደህንነት ጥበቃ ቴክኖሎጂ

image is here
image is here
image is here
image is here
image is hereቅድመ ታሪክ
ያካባቢ ደህንነት ጥበቃ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የተቋቋመበት አላማ አካባቢን በማይጎዳ መልኩ አረንጓዴ ልማትን ለማፋጠን እና ቀጣይነት ያለው እድገትን ለማስመዝገብ የአካባቢ ጉዳይ ቸል ሊባል የማይቻል በመሆኑ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ደረጃውን የጠበቀ ምርትን አምርቶ ተወዳዳሪ ለመሆን የአለም አቀፉ ገበያ የሚፈልገውን መስፈርት ሁሉ ማሟላት አስፈላጊ በመሆኑ፡ እና የአካባቢ ጉዳይ የትውልድ ጉዳይ ስለሆነ ይህ አስተሳሰብ በባለኢንዱስትሪው ውስጥ እንዲሰርፅ በማድረግ እና ምርት በማምረት ሂደት የሚፈጠረውን ማንኛውንም አካባቢን የሚጎዳ ነገር እንዴት ሳፈጠር ማስቀረት ወይም ሲፈጠር መጠኑን ማሳነስ እና አካባቢን ሳይጎዳ ለሌላ ጥቅም የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ለሌላ ጥቅም ማዋል ካልተቻለ ደግሞ አካባቢን የማይጎዳበት ደረጃ እስኪደርስ ድረስ የማምከኛ ዘዴዎችን መጠቀም እንደሚገባ በማስተማር፡ በማማከር እና በምርምር የማምከኛ ተቋማት (Treatment plants) እንዲቋቋሙ እና የንፁህ የአመራረት ዘዴ እንዲተገብሩ ከባለኢንዱስትሪዎቹ ጋር አብሮ ለመስራት ነው፡፡