የጫማ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬትአላማ
የጫማ አመራረት ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩቱ ውስጥ ካሉት አስርዳይሪክቶሬቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በጫማው ዘርፍ የውጪ ምንዛሪ ዕድገት የማስመዝገብ፣ለዜጎች ሰፊየ ስራዕድል መፍጠር፣ምርት ናምርታማነትማሻሻል፣የምርትጥራት ማሳደግ፣በብዛትና በጥራት የሰለጠነ የሰው ሀይል መፍጠር፣የኢንቨስት መንትማስፋፋት እና ሌሎች የልማትግቦችን ለማሳካትና የወጪ ንግዱ ላይ አወንታዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚያስችሉ ፕሮግራሞችን ቀርፆ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ተልእኮ
የዳይሬክቶሬቱ አላማ የፋብሪካዎችን ምርታማነት በማሳደግ፣ የጫማዎችን ጥራት በማሻሻልና ደረጃቸዉን የጠበቁ የአጭር እና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን በመስጠት የኢትዮጵያን የጫማ ኢንዱስትሪ በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግ ነዉ፡፡ የስራ ክፍሉ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ፣ ምርታማነትን በማሻሻልና የገበያ አማራጮችን በማፈላልግና በማስፋት ለዉጭ ምንዛሬ ግኝት፣ የሀገሪቱን በዘርፉ ያላት አቅም ጥቅም ላይ እንዲዉል ለማድረግና በዘርፉ የስራ እድል አንዲፈጠር የሰራል፡፡