የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ታሪክ

በሀገሪቱ ያለዉ የኢንዱስትሪ ልማት በጣም በአነስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ባለፉት አስርት አመታት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዉ ዘርፍ ለጥቅል አመታዊ የሀገር ዉስጥ ምርቱ ከ5 በመቶ በታች አስተዋጽኦ ሲያደርግ ነዉ የቆየዉ፡፡ ይህን የእድገት አካሄድ ለመለወጥና መንግስት ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ያለዉን ራዕይ እዉን ለማድረግ መንግስት ለቆዳዉ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቷል፡፡ የቆዳዉን ዘርፍ በዋነኛ ለመደገፍና የዘርፉን በአለም አቀፍ ገበያ ያለዉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግም የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩትን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 181/2002 አቋቁሟል፡፡