የቆዳ አልባሳትና ዕቃዎች ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬትሰለ ዳይሬከቶሬት

የኢትዮጵያ የቆዳ ምርቶች በአለም የቆዳ ምርቶች እሴት ሰንሰለት ዉስጥ ያለው ድርሻ አነስተኛ ሲሆን ወደ እሴት ሰንሰለቱ ዘልቆ ለመግባት በጥረት ላይ ይገኛል፡፡ የቆዳ አልባሳትና እቃዎች አመራረት ቴክኖሎጂ ዳይክቶሬት ባለው የሰው ኃልና አቅርቦት ንኡስ ዘርፉን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል የሚከተሉትን አበይት ተግባራት ያከናውናል፡፡

ቆዳን ወደ ተለያዩ ዘመናዊና ሳቢ ምርቶች እንቀይራለን
ቆዳ በረጅም እድሜዉና እንደፈለገ የመተጣጠፍ ባህሪዉ ምክንያት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለማምረት ከሚያገለግሉ ቁሶቸ መካከል አንዱ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በቆዳ ላይ እንደ ተጣጣፊና ለመለበሰ የሚችል የኤሌከትሮኒክስ ፣ ተለባሽ የሆነ የባዮ ሜትሪክ አልባሳትን የመሳሰሉ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች የታገዘ አመራረት ደረጃ ላይ አልተደረሰም፡፡ ይህ የሆነዉም ቆዳ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ያልሆነ ቁስ በመሆኑ ነዉ፡፡ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ ቁሶችን ለማምረት እንዲቻል ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ ባህሪ ያላቸዉ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ታዲያ እነዚህን ስማርት የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ምርቶችን ለማምረት እንዲቻል ቆዳ የኤሌክትሪክ አስተላላፊነት ባህሪን ሊላበስ የሚችልበትን ዘዴ በማጥናት ላይ አንገኛለን፡፡ ይህም የቆዳን የኤሌክትሪክ አስተላላፊነት ባህሪ እስከ 7 ነጥብ 4 S/cm ለማሳደግ ያስችላል፡፡ ኤሌክትሪክ አስተላላፊ የሆነ ቆዳ በጣት የሚነካ እስክሪን ያላቸዉን የኤልክትሮኒክስ ምርቶች / እንድ ስማርት ስልኮች፣ታብሌቶች፣አይ ፖዶች የመሳሰሉትን/ለመጠቀም የሚያስችል ጓንትና ስማርት አልባሳትን ለማምረት ያስችላል፡፡

Influence of sewing threads on seam pucker of sheep nappa leather
በስፌት ወቅት የሚያጋጥመዉ የቆዳ የመሸብሸብ ባህሪ የቆዳ ምርቶቸን ጥራት በመጉዳት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለዉ፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት በወነኛነት ለመሸብሸብ መንስኤ የሆነዉን ጉዳይ ለመለየትና sheep nappa leather መፈትሄ የማሰቀመጥ ስራ ተከናዉኗል፡፡ በዚህ ጥናት ለቆዳ ምርቶች ጠርዝ፣ ለመለጠጥ አቅም፣ ለመለጠጥ ባህሪና የድር አይነት ለመሸብሸብ ችግር መንሰኤ የሆኑ ነገሮችን በመለየት መፈትሄ ለማስቀመጥ ተሞክሯል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ከመሸብሸብ ጋር ተያይዞ ያሉ የጥራት ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ፡፡

ተጠባቂ የጥናትና ምርምር መስኮችና መተግበሪያ እቅድ
  • የቆዳን ባህሪ በቴክኖሊጂ ለታገዘ ዘመናዊ ምርት ለማምርት ወደ ሚያስችል ደረጃ ማሳደግ

  • ከቆዳ ተረፈ ምርት ከፍተኛ ዋጋ ያላቸዉን ምርቶች ለማምርት የሚያስችሉ አዳዲስ ቁሶችን ማልማት

  • የተሻሻሉ የምርት ዉጤቶቸን ከቆዳና ከጨርቃጨርቅ ስብጥር ለማምረት የሚያስችሉ ምርቶችን መለየትና ማልማት

  • መሳሪያዎችን የመለየት፣ደረጃ የማዉጣት ፣ ምርታማነት ማሻሻል

  • የኢትዮጵያ የቆዳ አልባሳትና እቃዎችን ምርቶች ደረጃ መለየትና ማዉጣት