የግብይት ድጋፍ ዳይሬክቶሬት


የዳይሬክቶሬቱ አጠቃላይ አላማ
የዳይሬክቶሬቱ አጠቃላይ አላማ የተለያዩ የግብይት ድጋፍ እስትራቴጂዎችን በመንደፍ የቆዳ እና የቆዳ ዉጤቶች ኢንዱስትሪዉ ዘላቂ ገበያ እንዲኖረዉ ማስቻል ነዉ፡፡

ዝርዝር አላማ
  • አዳዲስ ገበያዎችን ማጥናትና ሰብሮ ለመግባት የሚያስችል እቅድ ማዘጋጀት
  • ኢንዱስትሪዎች ዘላቂ ገበያ እንዲኖራቸዉ ለማረጋገጥ የሚያስችል የግብይት እስትራቴጂ ማዉጣት
  • ኢንዱስትሪዉ ቀድሞ የገባባቸዉ ገበያዎች ዘላቂ እነዲሆኑ የሚያችል ዝርዝር ጉዳዮችን ማቀድና ተግባራዊ ማድረግ
  • በኢንዱስትሪዎች የኤክስፖርት እቅድ ላይ በመመርኮዝ የጥሬ እቃ፣የመለዋወጫና የማምረቻ ቁሳቁሶች እንዲሟሉላቸዉ ድጋፍ ማድረግ
  • በጥያቄዎች ላይ ተመርኩዞ ኤክስፖርት ለማመቻቸት የሚያስችል የኤክስፖርት ድጋፍ ማዕቀፍን ተግባራዊ ማድረግ