የግብይት ድጋፍ ዳይሬክቶሬት

አገልግሎቶች

ዋና ዋና አገልግሎቶች፡
  • የአቅርቦት (የግብዓት፣ የፋይናንስ፣ የቆዳ ኬሚካል አክሰሰሪና ኮምፖነንቶች ) ድጋፍ እና
  • የገበያ ማፈላለግና ማስተሳሰር ድጋፍ፣
  • የኤክስፖርት ፋሲሊቴሽን ድጋፍ
  • የፕሮሞሽን ድጋፍ፣ ናቸው፡፡
ዳይሬክቶሬቱ በወጪ ንግድ ላይ ትኩረት አድርገው ለሚሰሩ የቆዳ፣ የጫማ፣ እና የቆዳ ውጤቶች ፋብሪካዎች ከዘርፉ ባለድርሻ አካላትና አስፈጻሚ መ/ቤቶች ጋር በቅርበት በመሆን የሚያጋጥሙ ችግሮችን የመፍታት፣ ለቆዳና ቆዳ ውጤቶች ምርቶች የውጭ ገበያ የማፈላለግና የማስተሳሰር፣  በምርት ማልማት የተሰሩ አዳዲስ ምርቶችን የማስተዋወቅ፣ ለፋብሪካዎች የጥሬ ዕቃ፣ የስራ  ማስኬጃና የውጭ ምንዛሪ፣ የቆዳ ኬሚካልና ሌሎች ግብዓቶችን አቅርቦት ድጋፍን የማመቻቸት፣ እንዲሁም ፋብሪካዎች ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ ሲልኩም ሆነ ጥሬ ዕቃ ከውጭ ሲያስገቡ በጉምሩክ፣ በባንክ፣ በሎጂስቲክስ የኤክስፖርት ፋሲሊቴሽን ድጋፍ ይሰጣል፡፡