ትምህርትና ስልጠና

image is here
image is here
image is here
image is here
image is here
image is here
image is here


ስለ ትምህርትና ስልጠነና

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የቆዳ ዘርፉን የሰለጠነ የሰዉ ሀይል ልማት በበላይነት እየመራ ይገኛል፡፡ ኢኒስቲትዩቱ በዘርፉ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ማንኛዉንም የስልጠና አይነትና መስክ ለማቅረብ ሁሌም ይተጋል፡፡ ከአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር በቆዳ አመራረት ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ድግሪ ስልጠና ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም በኢንሰቲትዩቱ በራሱ የቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠናዎችን በተለያዩ መስኮች ይሰጣል፡፡

በቆዳ ኢንዱስትሪዎች ያለዉን በመካከለኛና ከፈተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰዉ ሀይል ክፍተት ለመሙላት በጫማ አመራርት ቴክኖሎጂ፣ በቆዳ አመራረት ቴክኖሎጂና በቆዳ አልባሳትና እቃዎች አመራረት ቴክኖሎጂ የቴክኒክና ሞያ እንዲሁም የአጫጭር ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም አለም አቀፍ ደረጃቸዉን የጠበቁ እንደ ሞዴል የቆዳ ፋብሪካ፣ ሞዴል የጫማ እና የቆዳ እቃዎችና አልባሳት ፋብሪካዎች ያሉ የማሰልጠኛ ፋሲሊቲዎች በተጨማሪም ምቹ የማሰልጠኛ ስፍራዎች አሉት፡፡

ከተመሰረተበት ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ የቆዳ ንዱስትሪዎችንና የምስራቅና ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ /COMESA/ አባል ሀገራት ቴክንሽያኖች፣ አመራሮች ፣ ስራ ፈጣሪዎችን አቅም የመገንባት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከአጋሮች ጋር ጠንካራ ጤናማ ግንኙነት ለመመስረትም የድርጅቶችን እስትራቴጂና አላማ በአግባቡ በመገንዘብና ስራቸዉን የሚያከናዉኑበትን አጠቃላይ የስራ ከባቢ በመረዳት እንቅስቃሴዎቸን ያደርጋል፡፡