ምርምርና ፍተሻ ላቦራቶሪ

image is here
image is here
image is here
image is here
image is here


የቆዳ ኢነዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት የላብራቶሪ አገልግሎት ለኢትዮጵያ የቆዳና የቆዳ ዉጤቶች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ጥራት ያለዉ አገለገሎት ለመስጠት የተቋቋመ ነዉ፡፡
  • የኢኒስቲትዩቱ የላብራቶሪ አገልግሎት የሚከተሉትን አላማዎች ለማሳካት ነዉ የተቋቋመዉ
  • ለደንበኞች ምርቶች የፍተሻ አገልግሎትን የመሳሰሉ ቴክኒካዊ ድጋፎችን በመስጠትና የምስክር ወረቀት በመስጠት የዉጭና የሀገር ዉስጥ ገበያ ደንበኞቻቸዉን ፈላጎት እንዲያረኩ ማስቻል
  • ከምርቶችና ቁሶች ጥራትና ደረጃ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሟቸዉን ችግሮች ለምፍታት ቴክኒካዊ የምክር አገልገሎት መስጠት
  • የጥራት ስርዓቶችን ለመዘርጋት ላብራቶሪዉን ለማስተዳደርና ለማሻሻል
  • በአለም አቀፍ ደረጃ (ISO/IEC17025:2005) መሰረት አገልገሎቱን መስጠት
  • የላብራቶሪዉን መሳሪያዎች በመጠቀም በቆዳና በቆዳ ምርቶች ላይ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ድጋፍ መስጠት
  • በኢንዱስትሪዉ የሚፈለገዉን የቴክኒክና የምክር ድጋፍ አገልግሎቶችን መስጠት
  • ለደንበኞች ዋና ዋና የላብራቶሪ አገልግሎቶችን ለመስጠት ወሳኝ የሆኑ መረጃዎችን ማሰባሰብና መያዝ
  • ለኢኒስቲተዩቱ ሰልጣኞች በስልጠና ወቅት የላብራቶሪ መሳሪዎቸ ሲያስፈልጉ እንዲጠቀሙ በማድረግ መደገፍ
  • ለ ISO 9001ዕ2005 የጥራት ደረጃ ዋነኛ አገናኝ የሆነዉን የእቃዎች የጥራት ተቋም QSAE ማስተዳደርና ህጎቹንና መመሪያዎቹን መከታተል እንዲሁም ማስተዳደር እንዲሁም ወደ ካሊብሬሽን አገለገሎት ደረጃ ማሳደግ
ከላይ የተዘረዘሩት የላብራቶሪዉ ግዴታዎች የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒሰቲትዩትን ላብራቶሪ የጥራት ማንዋል እንዲያዘጋጅ አስችሎታል፡፡ ይህም በISO/IEC 17025:2005 በአለም አቀፍ ደረጃዎች ሁለተኛ ዙር በ15-05-2005 በመለያ ቁጥር ዳይሬክቶሬቱ ለመከተል እንዲችል አድርጎታል፡፡

እዉቅና/አክርዲቴሽን/
በተቀመጠላቸዉ አላማ መሰረት ተግባራቸዉን እንዲወጡ ላብራቶሪዎች የግድ እዉቅና ወይንም አክዲቴሽን ሊሰጣቸዉ ይገባል፡፡ ይህም ማለት አንድ ላቦራቶሪ የተወሰኑ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለዉ የእዉቅና መብት አለዉ ማለት ነዉ፡፡ ይህ እዉቅናም /አክሪዴትድ ቦዲ/ የሚል ስያሜ ባለዉና የላብራቶዉን አቅም የሚያስተዳድር ፣ የሚከታተልና የሚያለማ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባለዉ አካል ሊሰጥ ይገባል፡፡ ይህ አካል ላብራቶሪዉ የእዉቅና ሰርተፍኬቱን ህጎችና መመሪያዎች ማሟላቱን ሲራጋግጥ ከሙሉ የእዉቅናዉ መብቶች ጋር እዉቅናዉን ይሰጠዋል፡፡

የኢኒስቲትዩቱ ላብራሪም በተለይ የሰዉ ሀይሉን ብቃት ለማሳደግ በጣልያንና በግብፅ ባለሞያዎቹ ስልጠና እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ በጣልያን የልማት ትብብር ኤጀንሲና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት UNIDO ድጋፍም SANAS ከተባለዉ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ የእዉቅና ሰጪ አካል አግኝቷል፡፡

የእዉቅና አሰጣጥ ስነ ስርዓቱም በደማቅ ሁኔታ በፈረንጆቹ ሰኔ 13 2009 በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ደኤታ ክቡር አቶ ታደሰ ሀይሌ፣ የወቅቱ በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር ራፋኤል ዴ ሉቲኦ ፣ የ ዩኒዶ ተወካይና የክልሉ ተወካይ ፣ ዶ/ር ዴቪድ ቶሚ ፣ የጣልያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ሚስተር ጆርጅ ስፓራቺ፣ የSANAS ከፍተኛ ሀላፊ ሚስተር ማፎ ፎኢኔ ፣ የዩኒዶ ከፍተኛ የኢንዱስትሪ ልማት ኦፊሰር ሚስስ ኦሬሊያ ካላብሮና ሌሎች በርካታ እንግዶች በተገኙበት ተከናዉኗል፡፡